ቀጣይ ወደ ተግባር ይገባሉ የተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች

ቀጣይ ወደ ተግባር ይገባሉ የተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች
May 2, 2020 No Comments Uncategorized Ethioadmin

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ታማሚዎችና ምልክቱ የሚታይባቸው ሰዎች ባሉበት ቦታ ሆነው የሚመዘገቡበት የሞባይል አፕሊኬሽንና ዌብ ሳይት መስራቱን አስታውቋል፡፡
የሞባይል አፕሊኬሽሽኑ በቫይረሱ የተያዙትም ሆነ ምልክቶች የሚታዩባቸው መመዝገብ የሚመዘገቡበትና በአከባቢያቸው በቫይረሱ የተያዙም ሆነ የተጠረጠሩ ሰዎች መኖራቸውን መረጃ የሚሰጥ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ማንነትና ያሉበትን ቦታ ለዋና ማዕከሉ መረጃ ይሰጣል፡፡
በዚህ አፕሊኬሽን የተመዘገቡ ሰዎች የኢንተርኔት አገልግሎት በማይገኝባቸው ቦታዎች ሲንቀሳቀሱ እንቅስቃሴያቸውን መመዝገብ የሚችል አፕሊኬሽን ሲሆን ቫይረሱ በሚገኝባቸው ጊዜም የተነካኳቸው ሰዎችና የሄዱበትን ቦታ ለመለየት ያስችላል፡፡ ይህም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የነበራችውም ንክኪ እና የቆዩባቸው ቦታዎች ለማወቅ የሚያደርገውን ምርመራ እና የማጣራት ስራ የሚያቀል ይሆናል።
በተቋሙ የበለጸገው ዌብሳይት ደግሞ ሰዎች ምልክቱ ከታየባቸው ጊዜ ጀምሮ በዌብሳይቱ በመግባት የሚመዘገቡበትና በየጊዜው ያሉበትን ደረጃ የሚያሳውቁበት ነው፡፡ ይህም በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲመዘገቡ የተመዘገቡበት አከባቢ ጭምር የሚጠቁም ነው ተብሏል፡፡
መንግስት በየአከባቢው ያለው የቫይረሱ ስርጭት ምን ደረጃ ላይ እንደሆነ ለመለየትና እንደአስፈላጊነቱም አጠቃላይ ምርመራ ለማድረግ የተባለው ይህ የፈጠራ ሥራ የበለጸገውን አፕሊኬሽን ሁሉም ዜጋ በሞባይል ስልኩ ላይ መጫን ይጠበቅበታል፡፡ ዜጎች ይህንን ተግባራዊ እንዲያደርጉም የሚመለከታቸው አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ባለሞያዎቹ አሳስበዋል፡፡

About The Author

Leave a reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *