ላለፉት ጥቂት ወራቶች ሰራተኞች በቤት ሆነዉ ሥራዎች እንዲሰሩ በመደረጉ እና የሳይበር ጥቃት ከፍ ማለቱን ተከትሎ የአይቲ ባለሙያዎች ከፍተኛ የስራ ጫና ዉስጥ መሆናቸዉን የኢቫንቲ Ivanti ጥናት ጠቆመ፡፡
የሳይበር ደህንነት ማስጠበቂያ ምርት አቅራቢዉ ‘ኢቫንቲ’ በጥናቱ 1,600 የኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ ኤክስፐርቶችን ያሳተፈ ሲሆን ባለሙያዎቹ ሰራተኞች በቤታቸዉ ሆነዉ እንዲሰሩ መደረጉ ለከፍተኛ የስራ ጫና መዳረጋቸዉን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም የአይቲ ባለሙያዎች የሥራ ጫና በ37 በመቶ ማደጉን ተነግሯል፡፡
የኮቪድ-19 ከተከሰተ ወዲህ የሳይበር ደህንነት ስጋት የጨመረ ሲሆን አጥፊ ተልእኮ ያላቸዉ ኢ-ሜይሎች 58 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ፣ የሰራተኛ ያልተጣጣመ የአጠቃቀም ስርዓት መኖር 45 ከመቶ እንዲሁም የሶፍትዌር የጥቃት ተጋላጭነት 31 ከመቶ ጭማሪ ታይቷል፡፡
ባለሙያዎችን ጫና ውስጥ ከከተታቸዉ ሌሎች ጉዳዮች መካከልም ከቪ.ፒ.ኤን ጋር የተያያዙ ጉዳዮች (74%) ፣ የቪዲዮ ኮንፈረንስ (56%) ፣ የባንድዊድዝ /bandwidth/ መስተጓጎል (48%) ፣ የይለፍ-ቃል ማስጀመሪያ (47%) እና ከመልእክት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች (47%) መሆናቸዉ ተጠቅሷል፡፡
የኢቫንቲ የሳይበር ደህንነት ሀላፊ የሆኑት ፊል ሪቻርድስ በበኩላቸው የኮቪድ 19 መከሰት እና ሰራተኞች በቤታቸዉ ሆነዉ መስራት መጀመራቸዉ በአይቲ ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት ላይ ያልተለመደ ፍላጎት እንዲከሰት እና እንዲጨምር ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡ ምንጭ፡ ኢንፎሴክ ማጋዚን