ትዊተር ሠራተኞቹ እስከወዲያኛው ከቤት እንዲሠሩ ወስኗል።

ትዊተር ሠራተኞቹ እስከወዲያኛው ከቤት እንዲሠሩ ወስኗል።
May 13, 2020 No Comments Uncategorized Ethioadmin

ዋና መሥሪያ ቤቱን ሳን ፍራንሲስኮ ያደረገው ትዊተር፤ አምስት ሺህ ተቀጣሪዎች ያሉት ሲሆን፤ ላለፉት ሁለት ወራት ከቤት ሲሠሩ ነበር።

ተቀጣሪዎቹ ከቤት መሥራታቸው ፍሬያማ መሆኑን ያስተዋለው ትዊተር፤ ከዚህ በኋላ ሠራተኞቹ ወደ ቢሮ መሄድ እንደማይጠበቅባቸው አስታውቋል።

ከቤት ሥሩ የተባሉት ተቀጣሪዎች፤ የሥራ መደባቸው ከቢሮ ውጪ እንዲሠሩ የሚደቅድላቸው ናቸው።

“ሠራተኞቻችን ከቤት እየሠሩ ውጤታማ መሆናችንን አይተናል፤ ስለዚህ ተቀጣሪዎቻችን ከዚህ በኋላ ወደ ቢሮ ሳይመጡ መሥራት ከፈለጉ ሁኔታዎችን እናመቻችላቸዋለን” ሲል የትዊተር መስራችና ኃላፊ ጃክ ዶርሲ ለሠራተኞቹ ኢሜል ልኳል።

የሥራ መደባቸው ከቤት ለመሥራት የማያመቻቸው ሠራተኞች ደግሞ የፊታችን መስከረም ወደ ቢሮ ይመለሳሉ ተብሏል።

ፌስቡክ እና ጉግልም ተቀጣሪዎቻቸው ይህን ዓመት ከቤት እንዲሠሩ መፍቀዳቸው ይታወሳል።

ትዊተር በመላው ዓለም 35 ቢሮዎች አሉት።

About The Author

Leave a reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *