ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ ነው

ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ ነው
May 14, 2020 No Comments Uncategorized Ethioadmin


የኢትዮጵያ ኤሌክትክ አገልግሎት ካሉት አጠቃላይ ደንበኞች ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ናቸው፡፡ ብዛታቸውም 2.48 ሚሊዮን ደርሷል፡፡

ሆኖም በተለያየ ጊዜ ከቆጣሪ ንባብ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ ተቋሙ አዲስ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አጠናቋል፡፡

Common meter reading instrument (CMRI) የተባለው ይህ ቴክኖሎጂ፤ ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓትን በማስፈን የቆጣሪ ንባብ ጥራት ችግርንና ግምታዊ አሞላልን ለማስቀረት የሚያስችል ነው፡፡ ይህንን የሚተገብሩ ባለሞያዎችም አስፈላጊ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡

CMRI ቴክኖሎጂው በ416 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወጪ በቁጥር 2000 የተገዛ ሲሆን፤ ሙሉ ለሙሉ ወደ ትግበራ ከመግባቱ በፊት ከያዝነው ግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ በመላው ሃገሪቱ በተመረጡ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በሙከራ ደረጃ ይተገበራል፡፡

የዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ሂደቱ በሚተገበርበት ወቅት የማንበቢያ መሳሪያው የቆጣሪ አንባቢው ደንበኛ ቤት መድረሱ በGPS በማረጋገጥ የንባብ መሙያው ሳጥን (Box) አረንጓዴ በማሳየት እንዲሞላ ይፈቅዳል፡፡ አንባቢው በቦታው ካልተገኘ የንባብ መሙያው ሳጥን (Box) ቀይ ስለሚያሳይ፤ ግዴታ አንባቢው በደንበኛው ቤት ሄዶ እንዲያነብ ያስገድደዋል፡፡ ይህም የቁጥጥር ስርዓቱ በማጠናከረ ብልሹ አሰራርን የሚከላከል ነው፡፡

የቆጣሪ አንባቢ በደንበኛ ቤት በአካል ተገኝቶ ትክክለኛ ንባብ መውሰዱ ወይም አለመውሰዱን ማረጋገጥ የሚችለው ይህ ቴክኖሎጂ፤ ቴክኖሎጂው በራሱ የሚያነብ፤ በእጅ ሲነበብ የሚፈጠሩ ስህተቶችን የሚያስቀርና በንባብ ወቅት ምን ያህል ደንበኞችን ተደራሽ መደረጉንም ማሳወቅ የሚችል ነው፡፡

ተቋሙ የCMRI ዘመናዊ የንባብ ስርዓት በሚተገብርበት ወቅት ከንባብ ጋር በተያያዘ የሚፈጠር ብክነትና ብልሹ አሰራር በከፍተኛ ሁኔታ ለመቅርፍ ያስችለዋል ተብሎ ይታመናል፡፡

About The Author

Leave a reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *